Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ገለፀ።

30-04-2026 22:07pm

መጋቢት 28/2014 ኮን፦ ማዘጋጃ ቤቱ ከድል በኋላ መደበኛ ስራውን የጀመረ ሲሆን ከተማዋን በማፅዳትና አንዳንድ የህዝብ የመገልገያ ቦታወችን በመጠገን የህዝቡ ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ግንባታዎችን ለማከናወን በዋድላ ወረዳ ስራና ስልጠና ፅ/ቤት ከተመረጡ ኢንተርፕራይዞች ጋር ዉል ለመውሰድ ከጫፍ መድረሱን የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አራጋው አያሌው ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ከመነሐሪያ እስከ ገበያው ድረስ 8 ሜትር ወርድና 483 ሜትር ቁመት ያለው የጌጠኛ ድንጋይ /ኮብል ስቶን / የማንጠፍ ስራ በ3,327,534.00 ብር ወጭ የሚገነባ ሲሆን ከመነሐሪያ እስከ የታቦት ማደሪያው ድረስ 370 ሜትር ርዝመት ያለው ደረጃውን የጠበቀ የውሃ መፋሰሻ ቦይ በር1,766,133.77 ብር ወጭ ይገነባል። ይህ ስራ ወደ ተግባር ሲቀየር ለተወሰኑ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ የከተማችንን ውበት ከፍ ስለሚያደርገው ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ከማዘጋጃ ቤቱ ጎን እንዲቆምና ቀና ትብብር እንዲያደርግ ስራ አስኪያጁ አቶ አራጋው ጠይቀዋል።

loading

loading

loading

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 12 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form