Staff

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአጋር አካላት ጋር የ2016 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ.ም የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እቅድ ትውውቅ አካሄደ።

30-04-2026 20:46pm

በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአጋር አካላት ጋር የ2016 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ.ም የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እቅድ ትውውቅ አካሄደ። ነሀሴ 29/2016 ዓ.ም (ዋድላ ኮሙዩኒኬሽን ) በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሀላፊ በነበሩት በአቶ አወቀ አለሙ የእቅድ አፈጻጸሙ እና የእቅድ ትውዉቁ ሰነድ ለውይይቱ ተሳታፊ አካላት ቀርቧል። ከቀረበው ሰነድ በመነሳት የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማዋ እድገት ፣መሰረተ ልማት ፣ጽዳትና ውበት ፣በከተማዋ ዙሪያ ህገወጥ የመሬት ወረራ ፣የውስጥ ለውስጥ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ እንዲሁም ከተማዋ ከተመሰረተች ረጅም እድሜ ያስቆጠረች ብትሆንም እድገቷ ግን ይኸነው የሚባል አደለም የሚሉ ጥያቄዎች አና ሀሳቦች ተነስተው በሚመለከተው አካል ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቶባቸዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙት ሁሉም የወረዳው አመራር ፣ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ሰራተኞች እና የመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። የዋድላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሁኔ ያለው ጌጤ ና የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲልማ ባዬ እንደገለጹት የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውን ገልጸው ኮን ከተማን ለማሳደግ ፣ለማልማት ፣ ጽዱና ውቡ አድርጎ ለመያዝ ከተፈለገ ቅንጅታዊ አሰራራችን በማጠንከር እና የሚመለከተው አካል የድርሻውን ወስዶ በመስራት፣ በማሰራት የድርሻውን ሲወጣ ብቻ እንደሆነ አመላክተዋል ። በመጨረሻም በኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች የምስጋናና የማበረታቻ የምስክር ወረቀት በመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ስም ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠና

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 13 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form