በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የወጣበት ቤት እየገነባ መሆኑን ስታወቀ።
30-04-2026 20:36pmበዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የወጣበት ቤት እየገነባ መሆኑን ስታወቀ። ግንቦት 13 /2017 ዓ .ም(ዋድላ ኮሙዩኒኬሽን)። በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የአርሶ አደሮቹን የመሬት ካሳ ግምት ክፍያ ጨምሮ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር የፈጀ ቤት እየገነባ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል ። በዋድላ ወረዳ የኮን ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ስራ አሰጋጅ አቶ ተክለአብ ገላነው አና የመሪማዘጋጃ ብቱ ህንጻ ሹም አቶ ተፈራ ተመስጌን እንደገለጹት እየተገነባ የሚገኘው ቤት በመሪማዘጋጃ ቤቱና በ01 ኮን ከተማ ቀበሌ ትብብር መሆኑን ጠቁመው የአበሳውን ድርሻ ይዞ እያስገነባ የሚገኘው መሪ ማዘጋጃ ቤቱ መሆኑን አብራርተዋል ። የመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ስራ አስጊያጅ አክለውም እየተገነባ የሚገኘው የቀበሌ ቤት ለለላቸው ለዝቅተኛ ነዋሪዎች እንደሆነ ገልጸው 14 ክፍል ያለውና 1 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሆኑን ገልጸው ለ14 ቤት ለለላቸው አባዋራ እና እመዋራ ችግር ይፈታል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል።





